TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የተስተካከለ

የHIV/AIDS ስርጭርት መጠን አሁንም አልቀነሰም!

በደቡብ ክልል የኤች አይ ቪ አድስ ስርጭርትን መቀነስ አልተቻለም፡፡ የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ መጠን ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የሆነው የደቡብ ክልል የቫይረሱ ስርጭት መጠን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰራም የስርጭት መጠኑን መቀነስ እንዳልተቻለ የክልሉ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የፕላንና ፕሮግራም ዳሬክተር አቶ ፍስሃ ለዕመንጎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ የነበረው የሰላም መደፍረስም ለቫይረሱ ስርጭት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ እንዲያንሰራራ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

ከ2011 ዓመታዊ ሪፖርት ስንመለከትም የስርጭት መጠኑ 4% ወይም ከመቶ ሰዎች ውስጥ አራቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ወስጥ የወንዶች የስርጭት መጠን 0.17 በመቶ፤ የሴቶች 0.25 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አቶ ፍስሐ ተናግረዋል፡፡ ምንም አንኳን የክልሉ ኤች አይ ቪ አድስ የስርጭት መጠን 0.4 በመቶ ቢሆንም በክልሉ በሚገኙ እንደንድ አከባቢዎች ላይ የስርጭት መጠኑ ወደ 1.9 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

የክልሉ ርእሰ መዲና በሆነችው #ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካበቢዎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሚካሄድባቸው ፋብሪካዎችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የበሽታው ተጋላጭነት #እየሰፋ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

Via #ኢትዮኤፍኤም

🏷ማስተካከያውን ለTIKVAH-ETHIOPIA የሰጡት የክልሉ ጤና ቢሮ የፕላንና ፕሮግራም ዳሬክተር አቶ #ፍስሃ_ለዕመንጎ ናቸው። ለኢትዮኤፍኤምም ማስተካከያውን ይድረስ ተብለናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1