TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሜቴክ⬇️

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እጅ የቀሩ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎችን በአስቸኳይ የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሆነው የመንግስት መስሪያ ቤት እንዲያስረክብ መንግስት መጠየቁ ተሰማ፡፡

ለስኳር ኮርፖሬሽን ተመልሰው ግንባታቸውን ለማጠናቀቅም ለውጪ ኮንትራክተር ይተላለፋሉ የተባሉት ሁለቱ የስኳር ፋብሪካዎች በለስ ቁጥር 1 እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ናቸው፡፡

በሜቴክ እጅ የቀሩ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች እስከ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ/ም ለስኳር ኮርፖሬሽን #እንዲያስረክብ መመሪያ ተላልፎ
እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁንና ከቀነ ገደቡ 13 ቀን ቢያልፍም እስካሁን የስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካዎቹን እንዳልተረከበ ተሰምቷል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሸገር fm 102.1 እንደተናገሩት ርክክቡን ለመፈፀም በተቋቋመው ቴክኒካል ኮሚቴ በኩል የሰነድና የፋብሪካዎች የግንባታ ሒደት ምን ላይ እንደደረሰ ጥናት ማድረግ ነበረባቸው ብለዋል፡፡

ስራው በተያዘው ጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ እስካሁን መረካከብ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

በሜቴክ ሪፖርት መሰረት የበለስ ቁጥር 1 የፋብሪካ ግንባታ 78 በመቶ፣ የኦሞ ኩራዝ ደግሞ 90 በመቶ ደርሷል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ለግንባታው ወጪ የተደረገው ግንባታው የደረሰበት ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ ስለመሆኑ እንዲሁም የሰነዶች ምርመራ በቴክኒካል ኮሚቴ እየተካሄደ መሆኑን አቶ ጋሻው ተናግረዋል፡፡

#ምርመራው ተጠናቅቆ ለሜቴክና ለስኳር ኮርፖሬሽን ቀርቦ መተማመን ላይ ሲደረስም ርክክብ ይፈፀማል ብለዋል፡፡

ይህም #በአስቸኳይ እንዲሆን መንግስት በጠየቀው መሰረት ስራዎቹ እየተፋጠኑ ነው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ከ7 አመታት በፊት ሜቴክ በአመት ከመንፈቅ ግንባታቸው አጠናቅቄ አስረክባቸዋል ብሎ ከጀመራቸው 10 የስኳር ፋብሪካዎች በቃሉ መሰረት አንዱንም ማጠናቀቅ ሳይችል ቀርቷል፡፡

በመሆኑም በሒደት 8 ፋብሪካዎችን አስረክቦ ለሌሎች የውጪ የስራ ተቋራጮች የተሰጡ ሲሆን የቀሩትን ሁለቱን ፋብሪካዎችም በቅርቡ
እንደሚያስረክብ እየተጠበቀ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia