TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #UAE በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት…
" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸውና በዕለቱ ለተማሪዎቹ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ የትምህርት ዕድል መገኘቱን መግለፃቸው ይታወሳል።

ከዚህ የትምህርት እድል ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት እድሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት የተገኘ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎቹ ከመስከረም/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲማሩ መመቻቸቱን ገልጿል።

ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት #የእንግሊዝኛ_ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንዲቆዩ የሚሰራ መሆኑን ገልጿል።

የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎቹም እንዲሁም እንደ አጠቃላይ ለሀገር በጣም ጥሩ እድል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች #እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም ሲል አሳውቋል።

ተማሪዎቹ መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ ?

- የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።

- አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን  የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በዓለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።

- ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ፦ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።

- ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በ1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።

- ዛይድ ዩኒቨርስቲ ፦ በ1998 የተመሰረተና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስመ ጥር የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው።

https://www.topuniversities.com

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia