TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🍲 " የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል " 🍲 ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪ የምግብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ፤ " የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል ያለውን ብሉ " አይነት ማስታዎቂያዎች መለጠፋቸውን ተከትሎ በበርካቶችን አነጋግሯል። ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ምንድነው የሚሉት ? - " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ #ከመጨመሩ…
#Update

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ በማህተም ተደግፎ ስለተለጠፈው " የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል ስለዚህ የሜኑ ማሻሻያ አድርገናል " የሚለውን ማስታወቂያ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ተቋሙ በመግለጫው ምን አለ ?

- " ከዚህ ቀደምም ቢሆን በየወቅቱና እንዳስፈላጊነቱ ' የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' ሲደረግ ነበር። "

- " አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ዩኒቨርሲቲው ያደረገውን የምግብ ማሻሻያ ሜኑ አስመልክቶ ተጨባጭነት የሌለውን መረጃ በማሰራጨት የተቋሙን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት እና የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። "

🔴 የትኞቹ ማህበራዊ ትስስር ገጾችና ሚዲያዎች ተጨባጭነት የሌለው መረጃ እንዳሰራጩ በግልጽ ስም አልጠቀሰም።

- " ከወራት በፊት የተደረገ የሜኑ ማሻሻያ ለማሳወቅ ማስታወቂያ ወጥቷል። ይህም የቀን ስህተት የነበረበት መሆኑን እና ' አዲስ የተደረገ የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' እንደሌለ እንገልጻለን። "

- " ኃላፊነት በማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ' ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው '  እየተባለ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በተቋሙ ዘንድ በፍጹም ተቀባይነት የለውም። "

🔴 የትኛው የማህበራዊ ትስስር ገጽ እና ሚዲያ ተማሪዎች ሊበተኑ ነው ብሎ እንዳሰራጨ ስም አልጠቀሰም።

- " ለተማሪዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ የተቋሙ አቅም በሚፈቅደው መጠን ጥራት ያለውን ምግብ በበቂ ሁኔታ በማቅረብ የመማር ማስተማር ሥራው እንዳይስተጓጎል አበክረን እንሰራለን። "

- " ለተማሪዎቹ ወቅቱ በሚፈቅደው አግባብ ጥራቱን የጠበቀ ምግብ ለማቅረብ የሜኑ ማሻሻያ ከማድረግ ያለፈ በተማሪ ምገባ ላይ አንዳች ጉዳት  አይፈጽምም። "

- " አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን ተቋሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በዩኒቨርሲቲው ላይ የከፈቱትና እየከፈቱ የሚገኙት የገጽታ ማጠልሸት ድርጊት በፍጹም ተቀባይነት የሌለውም፤ በህግ አግባብ ያስጠይቃል። "

🔴 እዚህም ጋር የትኞቹ እንደሆኑ በግልጽ ስም አልተጠቀሰም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከሰሞኑን በወላይታ ሶዶ እና በዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉትን ማህተም ያረፈባቸውን ተመሳሳይ ይዘት ስላላቸው ማስታወቂያዎች በተመለከተ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

ተቋማቱ ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ፥ " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል " ይላል።

ይቀጥልና ፥ " ተቋሟችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ነው " ሲል ይገልጻል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ ደግሞ " ባሉን የምግብ ጥሬ ዕቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም #እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል " ይላል።

ይህ በተመለከተ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ፥ ማስታወቂያውን ሆነ ሀሳቡን #እንደማያዉቁት በመግለጽ " ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አክብር ጩፋ ደግሞ ፤ " ሶሻል ሚዲያ ላይ  መረጃው ሲንሸራሸር እያየን ነው " ካሉ በኃላ ሁኔታዉን ለማጣራት #ማኔጅመንቱ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

@tikvahethiopia
😡560164🤔46😢43🕊42🥰16😱16🙏14😭14👏7