TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
<unknown> – Professor_Tasew__TIKVAH
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!

(አሐዱ ቴሌቪዥን - ኬላ ፕሮግራም)

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በዚህ ዓመት #እንደማያስመርቅ አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና በአሐዱ ቴሌቪዥን ከሚተላለፍ 'ኬላ' ከተሰኘ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ሐምሌ 4/2012 ዓ/ም በሚካሔደው የተማሪዎች ምርቃት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የማታ የመጀመሪያ ዲግሪ ፣ የ2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች ብቻ ይካተታሉ።

በተያያዘ ዜና የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ እንዳበቃ የገጽ ለገጽ ትምህርታቸውን እንደሚቀጥሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ይፋ አድርጓል።

የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ግን በበይነ መረብ ወይም ኦንላይን ተፈትነው ትምህርታቸውን የሚያጠናቀቁበት ሁኔታ ተቀምጧል ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia