TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነእፓ

በሀገሪቱ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶችን ለማስቆም “ ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ ! ” በሚል የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ ይዞ መቅረቡን አሳውቋል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፤ ሀገራችን በታሪኳ በርካታ በእርስ በእርስ ግጭቶችን ማስተናጓን ገልጿን።

ለ2 አመታት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር ክልሎች የተካሄደው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ህይወት መቅጠፉን አመልክቷል።

አሁንም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የቀጠለው የወንድማማቾች ጦርነት የወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ ገልጿል።

በየአካባቢው በተለኮሱ ጦርነቶች ሳቢያ ፦

- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን እንዳጡ፣ አካላቸው እንደጎደለ፤

- እድሜ ልካቸውን ያፈሩት ንብረት እና የሀገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ ሀብትም እንደወደመና እየወደመም እንደሚገኝ ገልጿል።

በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ያለ አሳዳጊ፣ አረጋውያን ያለ ጧሪ ፣ አያሌ ኢትዮጵያውያን ለርሀብ፣ ለእንግልት፣ ለስደት እና ለሞት መዳረጋቸውን ገልጿል።

በየአካባቢው የተከሰቱ ግጭቶች ማህበራዊ ግንኙነታች እንዲበጣጠስ፣ በዜጎች መካከል ጥርጣሬ እንዲነግስ፣ ማህበራዊ ትስስራችን እንዲላላ፣ ጥላቻ፣ እልህ፣ በቀል እንዲስፋፋ፣ ስጋት እና ጭንቀት በዜጎች ልቦና እንዲሰፍን ማድረጋቸውንም አመልክቷል።

ነእፓ፤ ጦርነት መቼም ቢሆን የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት የተሻለ አማራጭ አይሆንም ፤ የእርስ በእርስ ጦርነት አሸናፊና ተሸናፊ የሌለው የመጨረሻ ውጤቱ ሞት፣ ስደት፣ ስቃይ፣ ሀዘን ፣ የሀገር ድቀትና መፍረስ ነው ብሏል።

ላለፉት ዓመታት ሰላም እንዲሰፍን በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የሚገልጸው ነእፓ ሀገራችንን ለክፉ ችግር፣ ህዝባችንን ማባሪያ ለሌለው ሰቆቃ የዳረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ “ #ኢትዮጵያ_በልጆቿ_ትታረቅ ” በሚል ስያሜ አዲስ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ መንደፉን ይፋ አድርጓል።

ዋናው ዓላማ በመንግስት እና ከመንግስት ጋር ነፍጥ አንግበው በሚፋለሙ ማናቸውም ኃይሎች መካከል በሀገር ሽማግሌዎች፣ በኃይማኖት አባቶች እና በሌሎች ታዋቂ ስብእናዎች አማካኝነት እርቅ ማውረድ እንደሆነ ገልጿል።

በቀጣይ ሂደቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች ይሰጣሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
🙏766😡160140🕊87🤔19😢18🥰15😱15😭15👏14