TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አፕቲትዩድ

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ከስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ዉጪ በሌሎች የትምህርት አይነቶች የፈተና አስተራረም ችግር አለመፈጠሩ ተገለጸ።

የሃገር አቀፍ ፈተናና ምዘና ኤጀንሲ ተማሪዎች ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ውጤትን መመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ከፈተናው የመልስ ቁልፍ ጋር ተያይዞ የነበረው እርማት ተጠናቆ በድረ ገጹ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መመልከት ይችላሉ ብሏል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሄር እንዳሉት የስኮላስቲክ ፈተናው ኮድ 21 እና 22 ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰዋል።

ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በድረ ገጽ መለቀቁን ጠቅሰው፥ የተለቀቀው ውጤት ያልተስተካከለው እንደነበር ገልጸዋል። ለዚህም ቀደም ሲል በአጭር የፅሁፍ መልዕክት የተለቀቀውን መረጃ ማጥፋት የሌላ አካል ሃላፊነት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ከፈተናው ጋር ተያይዞ ለኤጀንሲው 10ሺህ ያህል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ አሁን ላይም ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ እስካሁን በሌሎች የትምህርት አይነቶች ችግሮች ያለመገኘታቸውን አስረድተዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እርማት ሃምሌ 20 ቀን 2011 መጠናቀቁን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ፈተናው ይፋ እስከሚደረግ ድረስ ባሉት ጊዜያትም መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ የማጣራት ስራ ሲሰራ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia