TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች። የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ…
" ... ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅዱ ገና ከአሁኑ ተጽእኖ እያሳደረብን ነው " - አይርላንድ

ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ #ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ #አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ መሆኑ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀምሯል።

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል።

የሀገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80% የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ መሆኑን ገልጿል።

የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች።

ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙ እና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia