TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ያከማቸው ሾፌር በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ #አንገሶም_ገብረሩፋኤል የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ዓ.ም አንቀጽ 21/ለ/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ከሚያገኘው ገቢ ጋር የማይመጣጠን ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

የወንጀሉ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፈጥሮ ደራሽ ዳይሬክቶሬት አሽከርካሪ በመሆን
በሚኤሶ፣ አዋሽና ናዝሬት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ደሞዝ ተቀጥሮ ሲሰራ በነበረበት ወቅት በመንግስት ስራው ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር በማይመጣጠን ሁኔታ ከኢትጵያ ንግድ ባንክ ሚኤሶ እና ጀሞ
ቅርንጫፍ በተለያዩ ጊዜያት በስሙ በከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ውስጥ ብር 542,087.74 (አምስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ሰማንያ ሰባት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም ) እንዲሁም በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 225,100.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ አምስት ሺህ ብር) በአጠቃላይ ግምቱ 767,187.74 (ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር ) ያለአግባብ ያከማቸ በመሆኑ በፈጸመው ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ የሰዎችና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክርና መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ አለመኖሩን እንደ ቅጣት ማቅለያነት በመያዝ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እና አምስት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር እንዲወረስ በማለት ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia