TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ የተሾሙት የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር ጅግጅጋ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አቶ ሙስጠፋ ከ11 አመት በኅላ ነው ወደ ክልሉ የተመለሱት።

በሌላ በኩል⬇️

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው #አስቸኳይ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሣኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ አቶ #ሙስጠፋ_መሐመድን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡

አቶ ሙስጠፋ የርዕሰ መስተዳድሩ ስራንም ሸፍነው ይሰራሉ፣ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ይሆናሉ ተብሏል፡፡

በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የቀድሞ አመራሮችን ጨምሮ ሰባት ግለሰቦች #ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ሊቀመንበር አቶ አበራ ባዬታ #መልቀቂያ አስገብተዋል:። ይህንኑ ተከትሎ የፖርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት #አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዳል፡፡የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አበራ ባዬታ ዛሬ ለኢቢሲ እንዳስታወቁት ማዕከላዊ ኮሚቴው በሚያደርገው ጉባዔ የመልቀቂያ ጥያቄውን መርምሮ ውሳኔ መስጠት ዋነኛ አጀንዳው ይሆናል፡፡የአመራር እጦት ችግሮች በፓርቲው ውስጥ መኖራቸው ተደርሶበታል ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፡፡ ለፓርቲው ተተኪ ሊቀመንበር መምረጥና በተጓደሉ ሥራ አስፈጻሚዎች አባላት ምትክ ምርጫ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት #አስቸኳይ_ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል፡፡

ሌሎችም ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ ይወያያል ብለዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ሲኖዶስ የፊታችን ረቡዕ #አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ዛሬ አሳውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ጥሪ ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
🙏1.86K👍401👎10896🕊68🤔31😢11😱8🥰3