TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል እየተከተሉ አልጋ በመያዝ ስርቆት ሲፈጸሙ ነበር " - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ

የሲዳማ ክልል ጸጥታ ኃይል " ስፈልጋቸው የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ይዛለሁ " አለ።

በቁጥጥር ስር የዋለቱ ተጠርጣሪዎች ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል እየተከተሉ #አልጋ_በመያዝ ስርቆት ሲፈጹም የነበሩ እንደሆነ የጸጥታ ኃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ካሁን በፊት በተመሳሳይ አይነት መንገድ ስርቆት ፈጽመዉ ሀዋሳ ከተማን በመልቀቃቸዉ ሳይያዙ ቢቆዩም ከሰሞኑ ከተማውን ሲረግጡ ጀምሮ በተደረገ ክትትል መያዛቸዉን የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ " ከገንዘብ አንስቶ ስማርት ስልኮች ከባጃጅ እስከ መኪኖች ድረስ ተደራጅተዉ የሚዘርፉና ከሀገር ውጭ ዶላር ተመድቦላቸው የዘረፋ ተግባር የሚፈጽሙ መሆናቸውን " የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሀሚድ አህመድ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ በከተማው የተተከሉ ካሜራዎችና የተሰማሩ የጸጥታ አካላት ሲከታተሏቸዉ ቆይተዉ እንደተለመደው ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል በማረፍ የዘረፋ ተግባራቸውን ለመፈፀም ሲሞክሩ እጅ ከፈንጅ መያዛቸዉን አስረድተዋል።

ግለሰቦቹ እንዲህ ያለዉን ተግባር ለመፈጸም እንዲችሉ ከሁለት መቶ በላይ ማስር ቁልፎችን እንዲሁም ሲያዙ ህገወጥ የውጭ ሀገር ገንዘቦች እና በርካታ ስልኮች እንዲሁም የባንክ ቼኮች መያዛቸዉን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ጉዳያቸው በህግ ተይዞ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወንጀል ምርመራው እና የፍርድ ሂደቱንም ሆነ የተጠርጣሪዎችን ሰንሰለት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
👏357128😱32😡26😭15🙏13🤔12🕊12😢11🥰1