TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አልነጃሺ_መስጊድ

1ሺህ 441ኛ የአሹራ በዓል ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከውጭ የሚመጡ ምዕመናን በተገኙበት ከነገ በስቲያ በትግራይ አልነጃሺ መስጊድ በድምቀት ይከበራል። የአሹራ በዓል በእስልምና ሃይማኖት ወር በገባ በአስረኛ ቀን ጳጉሜን 4 ለፈጣሪያቸው ፀሎት በማድረግ የሚያከብሩት ነው። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና የኢትዮ-ነጃሽ የማልማትና የማስተዋወቅ ፕሮጀክት ትናንት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአሹራ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አልነጃሺ

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ ጥገና ባለመደረጉ የሶሀባዎች መቃብር በዝናብ እና በፀሀይ እየተደበደበ መሆኑ ተገለፀ።

ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አልፎም የዓለም ሙስሊሞች ታሪክ የሆነው ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጅድ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በውስጡ የነበሩ ቅርሶችም ተዘርፈው መወሰዳቸውን የአል ነጃሺ መስጅድ ኢማም እና አስጎብኚ  ተናግረዋል።

በጦርነቱ ምክንያት የንጉስ አል ነጃሺን ጨምሮ የ8 ሶኻባዎች የመቃብር ስፍራ ያለበት ቦታ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ በዝናብ እና ፀሀይ እየተደበደበ ከመሆኑም ባሻገር የመፍረስ አዳጋ እንደተጋረጠበት ኢማሙ ተናግረዋል።

በተጨማሪ የአል ነጃሺ መስጂድ ሚናራ በመሳሪያ የተመታ በመሆኑ በዝናብ ፍሳሽ እንደተቸገሩ ገልጸዋል።

ከቅርብ ሳምንታት በፊት በመንግሥት በኩል " የአል ነጃሺ መስጅድ በቱርክ መንግስት እድሳት እንደሚደረግ ቢገለፅም እስካሁን የመጣ አካል የለም " ሲሉ ኢማሙ ተናግረዋል።

በሌላ ዜና ፤ ሼህ ሙሀመድ አልሀሙዲን ለታሪካዊው የአልነጃሺ መስጂድ  ትራንስፎርመር በመቃጠሉ የተቋረጠውን የውሀ እና መብራት አግልግሎት ለማስቀጠል ጥገና ለማድረግ በሚድሮክ ኩባኒያ በኩል ቃል መግባታቸው በመጅሊስ ልዑካን ቡድኑ መስማታቸው እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የነጃሺ አካባቢ ነዋሪዎች ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ቶሎ ተፈፃሚ እንዲሆን ጠይቀዋል።

መረጃው የሀሩን ሚዲያ ነው።

@tikvahethiopia