TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ማህበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል። ሪፖርተር ጋዜጣ ከአገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ማኅበራት ያገኘሁት ባለው መረጀ ፤ የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወደ ትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ…
ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ጀምሯል ?
ከሳምንታት በፊት ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ሃገር አቋራጭ ትራንስፖርት በቅርቡ ይጀመራል ተብሎ ቢነገረም እስካሁን #አልተጀመረም።
በትግራይ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የስልክ፣ የባንክ ፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ቢጀመርም እስካሁ ድረስ የየብስ ትራንስፖርት አለመጀመሩ ተገልጿል።
የትግራይ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ፤ የመንገድ / የየብስ ትራንስፖርት እስካሁን ባለመጀመሩ ህብረተሰቡ ላይ ከባድ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየደረሰ ነው ብሏል።
የየብስ ትራንስፖርት አለመጀመሩ በርከታ ነዋሪዎች የሚጠቀሙበትን የየብስ ትራንስፖርት እንዳይጠቀሙ እንዳደረጋቸው እንዲሁም እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ እንደገደባቸው ተመልክቷል።
ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር አብዛኛው የክልሉ ነዋሪዎች በአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም እንደማይችሉ ተገልጿል።
ቢሮው ክልሉ የየብስ ትራንስፖርት ለማጀመር የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን የገለፀ ሲሆን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት እንዲጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።
" ትራንስፖርት የማስጀመር ድርሻው የፌዴራል በመሆኑ እሱን እየጠበቅን ነው " ሲል አክሏል።
ከሳምንታት በፊት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት ለማስጀመር ለማኅበራት መመሪያ ማስተላለፉን እና በሰላም ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እንደፈቀደ አገልግሎቱ እንደሚጀመር ማሳውቁ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል ፤ በጦርነት ምክንያት " ሰላም ባስ " ለሁለት ዓመታት አቋርጦት የነበረውን ከመቐለ ወደ ሽረ አገልግሎት መጀመሩን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
@tikvahethiopia

👍1.55K🕊195👎110❤65🤔30🙏29😢22😱16🥰12