TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ክልል ልዩ ቦታው ገርጅ ላስታ ሰፈር አካባቢ ከሌሊቱ 5፡00 ገደማ ባለቤቱን የገደለው ተከሳሽ በፈፀመው #አሰቃቂ የነፍስ ማጥፋት ወንጅል በእስራት ተቀጣ፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ #አለማየሁ_አየለ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539/1/ሀ የተመለከተውን ክልከላ በመተላለፍ የገዛ ባለቤቱን በእኔ ላይ ሌላ ወንድ ወደሻል በሚል ሰበብ ጭካኜ በተሞላበት ሁኔታ በያዘው ዱላ #ጭንቅላቷን ደጋግሞ በመምታትና እና የቀኝ እጇን በቢላዋ በመውጋት ቤቱን ቆልፎባት የሄደ በመሆኑ በተከሰተው ከፍተኛ የደም መፍሰስና በተፈፀመባት አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርምሮ በማጠራት ጥር 28 ቀን 2011ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛው በ21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia