ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን‼️
ኮማንደር #አለሙ_መግራ የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
ኮማንደር አለሙ መግራ ከዚህ በፊት የከተማ አስተዳድሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን አቶ ጌታቸው አስረስን በመተካት መሾማቸውን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮማንደር አለሙ መግራ ለ26 አመታት በፖሊስ ሙያ በተለያየ ሃላፊነት የሰሩና ያገለገሉ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ በአዳማ ፣ቢሾፍቱ ፣በሻሸመኔ ከተሞችና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ፖሊስ አዛዥ በመሆን አገልግለዋል።
በተጨማሪም የኦሮሚያ ትራፊክ ፖሊስ ሃላፊ በመሆንና ላለፉት 5 ወራት በሐረሪ ክልል መንግስት የክልሉ ምክትል ኮሚሽነር በመሆን ሰርተዋል።
ኮሚሽነሩ ሹመታቸውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ህዝብን በባለቤትነት በማሳተፍ ለህግ የበላይነት መረጋገጥና ለዘላቂ ሰላም መስፈን ቅድሚያ ሰተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከህብረተሰቡና እና ከፖሊስ ሰራዊቱ ጋር ሰፊ የውይይት መድረኮች የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኮሚሽነሩ አያይዘውም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ እስካሁን ለሰላም መስፈን ሲያበረክት የቆየውን ትብብርና እገዛ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ኮማንደር አለሙ መግራ በማኔጅመንትና በህግ የመጀመሪያ ድግሪና በሙያው የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia