#update በአዲስ አበባ ከተማ ህገ ወጥ ቤት ገንብተው የሚኖሩ ዜጎች በ2 ሳምንት ውስጥ ግንባታቸውን እንዲያፈርሱ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከክፍለ ከተማ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ዛሬ መክረዋል፡፡
በዚህም ህገወጥ ግንባታ የፈፀሙ አካላት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አፍርሰው ንብረታቸውን እንዲያነሱ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል፡፡
ይህ የማይሆን ከሆነ የከተማ አስተዳደሩ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እርምጃ እንዲሚወስድ ተናግረዋል፡፡
የህገ ወጥ ግንባታ በስፋት ይገኙባቸዋል የተባሉትና እንዲያፈርሱ የተጠየቀባቸው ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ጉለሌና የካ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡
Via #አሀዱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

" የመንግሥት ንብረትና ሐብት ለፓርቲ ሥራ ስለመዋሉ እንዲጣራልኝ ብጠይቀም ምላሽ አላገኘሁም " - ኢዜማ
" የመንግሥት ንብረትና ሐብት ለፓርቲ ሥራ እየዋለ ስለመሆኑ እንዲጣራልኝ ብጠይቀም ምላሽ አላገኘሁም ሲል " የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አስታወቀ።
ኢዜማ " ብልጽግና ፓርቲ መንግሥትን እና ፓርቲን ባለመለየቱ እሳየ ያለው ቸልተኝነት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት እንቅፋት ይሆናል " ብሏል፡፡
በተጨማሪ ፓርቲው ለፌደራል ዋና ኦዲተር የመንግሥት ንብረትና ሀብት ለፓርቲ ሥራ መዋሉ በኦዲት እንዲጣራ ቢጠይቅም አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ " ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመንግሥት ንብረት እና ሀብት ለፓርቲ ሥራ መዋሉን ጠቅሰን በኦዲት እንዲጣራልን በደብዳቤ የጠየቅን ቢሆንም እስከ አሁን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘንም " ሲል ገልጿል።
በተመሳሳይ ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም. ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ሥልጠና ከመንግሥት ካዝና ገንዘብ ወጥቶ መከፈል ስህተት መሆኑንና ሊታረም እንደሚገባ መግለጹን አስታውሷል።
" ይኼው ተግባር ከተጠናቀቀ ጥቂት ቀናት ባስቆጠረው ያለፈው ዓመት ብልፅግና ፓርቲ ከመንግሥት ንብረት የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸመ ነው " ሲል ፓርቲው ገልጿል።
" ብልፅግና ፓርቲ የመንግሥት ሥልጣንን እንደያዘ ፓርቲ እያሳየ ያለው ዳተኝነትም በሀገራችን እውን ሆኖ ማየት ለምንፈልገው የመድብለ ፓርቲ እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት መሆኑን በተደጋጋሚ በሚፈፅማቸው ስህተቶች እየተመለከትን ነው " ሲልም ተችቷል፡፡
ይህ ተግባር በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ ካልተወሰደ ለሀገር ዴሞከራሲ ግንባታ ወደሚበጅ ትክክለኛ አሠራር እና ልምምድ ካልተመለሰ በስተቀር የሚያመጣው ቀውስ እና ይዞ የሚመጣው መዘዝ ቀላል አይደለም ብሏል።
" የሚመለከታቸው ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሰሞኑን ብልፅግና ፓርቲ ለሥልጠና የተጠቀመበትን ሀብትና ንብረት በትክክል ወደ መንግሥት ካዝና መመለሱን እንዲያረጋግጡ " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
መንግሥትንና የሥራ ኃላፊዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ፣ የተቋቋሙ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትም በሀገር እና በሕዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና መንግሥትን ተጠያቂ እንዲያደርጉ እንዲሁም የሀገርን ሀብት ከሙስና እና ከምዝበራ እንዲታደጉ ሲል ፓርቲው ጠይቋል። #ኢዜማ #አሀዱ
@tikvahethiopia