TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መከላከያሰራዊት

"የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን #ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል!" - ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ
.
.
የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በቅርቡ የፀደቀውን የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ በመተግበር የሰራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ይህን ያሉት በተሻሻለው የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራዊቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ነው፡፡

ጀነራል ብርሀኑ በዚሁ ወቅት የሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሻሻል ከነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚራመድ ገለልተኛ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚረዳውም ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ ገለልተኛ እና ስራዎቹን እውቀትን መሰረት በማድረግ የሚሰራ የመከላከያ ሰራዊት መለዮውን እየቀየረ ነው ያሉት ጀነራል ብርሀኑ ከዚህ በኋላ የመከላከያ መለዮ ከተቋሙ አባል ውጪ ሊለበስ እንደማይችል እና በምንም ምክንያት ወደ ውጪ እንደማይወጣ ተናግረዋል፡፡

(የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር )

@tsegabwolde @tikvahethiopia