TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስራቅ ጎጃም‼️

በምስራቅ ጎጃም ዞን #ነዳጅና #ሲሚንቶ ጭነው ይጓዙ የነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተገልብጠው ንብረት መውደሙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ኢንስፔክተር #ጎበዜ_ይርሳው ለኢዜአ እንደተናገሩት አደጋው የደረሰው ከሱዳን አዲስ አበባ ነዳጅ ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ትናንት በመገልበጡ ነው፡፡

በአደጋው ቦቲው 47ሺህ 950 ሊትር ቤንዚን ጭኖ ከነተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በእሳት መጋየቱን አስታውቀዋል፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 7139 ተሳቢ 10704 ኢትዮጵያ የሆነ መኪና የመገልበጥ አደጋው የደረሰው በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ትግዳር ቀበሌ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪው #በቁጥጥር ሥር ውሎ  የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑንም ኢንስፔክተር ጎበዜ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ከአዲስ አባባ ወደ ቡሬ ኢንዱስትሪያል ፓርክ  ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 75260 ተሳቢ 18 029 ኢትዮጵያ የሆነ ተሽከርካሪ መኪና 400 ኩንታል ሲሚንቶ እንደጫነ በማቻከል ወረዳ በአማሬ ቀበሌ በመገልበጡ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

የካቲት 6/2011 ከሌሊቱ ሰባት ስአት በደረሰው የመገልበጥ አደጋም በተሽከርካሪውና በተጫነው ሲሚንቶ   ምርት ጉዳት ደርሷል፡፡

አሽከርካሪውም የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል ብለዋል።

የሁለቱም ተሽከርካሪዎች አደጋ ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የቡድን መሪው አስታውቀዋል። 

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia