#ትፈለጋለች
በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አንዲት እንጀራ እናት ሁለት ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደሏ እየተፈለገች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ስለጉዳዩ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ምን አሉ ?
ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ፦
" ወንጀሉ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም. በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሦስተኛ ቡራዩ በሚባል ስፍራ ነው።
ወንጀሉ የተፈፀመው ሌሊት ነው። ሁለት ሕጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ በእንጀራ እናታቸው ተገድለዋል ተገኝተዋል።
ተጠርጣሪዋ ነጋሴ ከበደ ብሩ የምትባል ስትሆን፣ የባለቤቷን ሁለት ልጆች አንገታቸውን ቀልታ፣ በተኙበት ብርድ ልብስ አልብሳ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣለች። "
የልጆቹ አባት የሆኑት አቶ ጌታሁን ባልቻ ምን አሉ ?
በአካባቢው የሚገኝ ቄራ የሚሰሩ ሲሆን ግድያው በተፈፀመበት ዕለት ማምሻውን ከባለቤታቸው ጋር በልጆቻቸው ጉዳይ ተነጋግረው እንደነበር ገልጸዋል።
አቶ ጌታሁን ባልቻ ፦
" በልጆቼ ጉዳይ ተነጋግረን ነበር። በዚህም ምክንያት እንለያይ ተባብለን፤ እርሷም ‘እኔ እሄዳለሁ፣ አንተ እዚህ ትኖራለህ’ አለችኝ።
ምሽት ላይ ስንነጋገር ዛቻም ሆነ ለእንደዚህ አይነት አሰቃቂ ድርጊት ያበቃል ብዬ የምጠረጥረው ጠቋሚ ነገር አላየሁም።
ሌሊት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ወደ ቤት ስመለስ የቤቱ በር ክፍት ነበር። ወደ ውስጥ ስገባ እሳት ይነዳል። ልጆቼን አልጋ ላይ ሳያቸው ጭሱ አፈነብኝ ብዬ ሮጬ ወደ ውጪ አወጣኋቸው። በወቅቱ ትልቁ ልጄ ተቃጥሏል። ትናሿ ልጄንም አወጣኋት። ወደ ውጪ ካወጣኋቸው በኋላ እነርሱ ላይ ወድቄ ራሴን ሳትኩኝ።
ልጆቼን መጀመሪያ ሳያቸው በሕይወት ያሉ መስሎኝ ነበር ፤ ያሟሟታቸውን ሁኔታ ራሴን ከሳትኩበት አንድ ቀን በኋላ ነው ከአካባቢ ነዋሪዎች እና ከፖሊስ የሰማሁት።
ልጆቼን ማሳደግ እፈልጋለሁ እንለያይ አልኳት. . . እኔ እሄዳለሁ አንተ እዚህ ትኖራለህ አለችኝ። ይህንን ብቻ ነው የተናገረችኝ። እንደዚህ ዓይነት ድርጊት በልጆቼ ላይ፣ ቤተሰቤ ላይ፣ እንስሳትም ላይ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም። "
በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት የአቶ ጌታሁን ልጆች አንደኛው የ13 ዓመት ወንድ ሲሆን፣ ሌላኛዋ ደግሞ የ4 ዓመት ተኩል ሴት ናቸው።
ሁለቱም አንገታቸው ተቀልቶ ነው የተገደሉት።
አቶ ጌታሁን በ2013 ዓ.ም የልጆቻቸውን እናት በሞት ካጡ በኋላ ባለፈው ታኅሣሥ ነበር ከተጠርጣሪዋ ጋር የተጋቡት።
ሲጋቡም የልጆቻቸውን ሁኔታ ገልፀው፣ ተማምነው ነበር የተጋቡት።
ከዚያ በኋላ እዚያው ቡራዩ አካባቢ " ሽሮ ቤት " ከፍታ ስትሰራ ቆይታለች።
ነዋሪነቷም እዚያው ቡራዩ አካባቢ ኤጀርሳ ጎሮ የሚባል አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዋ እየተፈለገች ነው ...
ፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ የሁለት ህፃናትን ነፍስ ያጠፋችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እያፈላለጋት ይገኛል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ የቤተሰቦቿ አባላትም አሉ።
ከሰበታ እስከ አንቦ ድረስ ከተጠርጣሪዋ ጋር የሚመሳሰሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችም አሉ።
መረጃው #የቢቢሲ_አማርኛ እና የቡራዩ ፖሊስ ነው።
@tikvahethiopia