TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ አስታወቀ። ካቢኔው ህዳር 16/2016 ከሰዓት በኃላ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በከባድ የድርቅ አደጋ ለተጎዱ መርጃ የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያስረዳል።  ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ፤ በተለይ በሦስት ዞኖች ፣ 12 ወረዳዎችና 47 ቀበሌዎች…
#ትግራይክልል 

በትግራይ ላለፉት ሁለት አመታት የታየው የእርሻ ግብአት እጥረት ፣ ጊዜው ያልጠበቀ ዝናብ ፣ የአንበጣ መንጋ ወረራና የተካሄደው ጦርነት ተከትሎ በቂ የምግብ እህል ባለመገኘቱ በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች ደርቅ አጋጥሟል።  

ባጋጠመው ድርቅ ምክንያትም በርካቶች ለሞት ፣ ለረሃብና ለመፈናቀል ተዳርገው እንደሚገኙ ተነግሯል። 

የድርቅ ችግሩ ለማቃለል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሃብት የማሳባሰብ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ ማሕበራዊ ረድኤት ትግራይ (ማረት) ደደቢት ማይክሮፋይናንስ እያንዳንዳቸው ብር 10 ሚሊዮን በድምር 20 ሚሊዮን ብር መስጠታቸው የተቋሞቹ ሃላፊዎች ይፋ አድርገዋል። 

ተቋሞቹ የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከድርቅ ችግሩ ስፋት አንፃር በቂ ባለመሆኑ የአገር ውስጥና የአገር ውጭ ለጋሾች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። 

" ቫራይቲ " የተባለ የግል የንግድ ተቋም በበኩበደርቅ ለተጎዱ ወገኖች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጥቷል።

በትግራይ ካለው ድርቅ ጋር በተያያዘ የሰው ህይወት ከመጥፋቱ በተጨማሪ ሰዎች ቄያቸውን ለቀው ወደ ልመና መግባታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ መቅረታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ፎቶ - ድምፂወያነ
  
@tikvahethiopia