TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትዴት

ተቃዋሚው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ባካሄደው ውይይት ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና ቀጥሏል አለ። ህዝብን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉም ገልጿል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና መቀጠሉን እና ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ለውጥ እንዳልታየበት ገለጸ። 

“የትግራይ ህዝብ በጠላት ተከብበሃል እየተባለ በህወሓት ሽብር እና ፍርሃት እየተለቀቀበት ለግጭትም እንዲጋበዝ እየተገፋ ነው” ያሉት የትዴት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ “ችግሩ የጋራ በመሆኑ በትብብር ልንታገለው ይገባል” ሲል በአዲስ አበባው ውይይት ላይ አሳስበዋል። “ህዝቡ ህወሓት እንደሚለው ጠላት የለውም” ሲሉም ለተሳታፊዎቹ ተናግረዋል። 

“አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድህነት ውስጥ ነው” ያለው ትዴት በትግራይ ያለው ችግር ተባብሶ በመቀጠሉ “ሕወሃት በቃንየሚለው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል”  ብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲው በዛሬው የአዲስ አበባ ስብሰባው “ሶሻል ዴሞክራሲ” የፖለቲካ መርህን እንደሚከተል ለደጋፊዎቹ እና ለውይይት ተሳታፊዎቹ አስታውቋል። “ዴሞክራሲ እና ፍትሃዊነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እንድትገነባም የድርሻዬን እጥራለሁ” ሲል ቃል ገብቷል። 

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia