TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል፤ " ገብረ ጉራቻ " በ9 ቻይናውያን ላይ ጥቃት ተከፍቶ የአንድ ቻይናዊ ህይወት ማለፉ ይታወቃል።
ይህንን ጥቃት በተመለከተ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማረጋገጫ ሰጥቶ ለጥቃቱ መንግስት በህ/ተ/ም/ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀውን " ሸኔ " ቡድንን ተጠያቂ አድርጓል።
የክልሉ ኮሚኒኬሽን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጠው ቃል የሽብር ቡድኑ በቀን 22/05/2015 ዓ/ም ማታ በገብረ ጉራቻ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ በተጠና ሁኔታ በፈፀመው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ሲገደል ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ በቡድኑ #ታፍኖ መወሰዱን ገልጿል።
የገብረ ጉራቻውን ጥቃት በተመለከተ አዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ፤ በ9 ቻይናውያን ላይ ጥቃት ተከፍቶ አንድ ቻይናዊ መገደሉን መግለፁ ይታወሳል።
ኤምባሲው ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ስለጥቃት አድራሾቹ ማንነት ምንም ያለው ነገር አልነበረም።
ጥቃቱን ተከትሎ የቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ዜጎቹ #ለአደጋ_ከሚያጋልጡ ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ መስጠቱ አይዘነጋም።
@tikvahethiopia