TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETRSS1 #ታህሳስ10

ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያግዝና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚስችል መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደምትመጥቅም ተገልጿል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ትላንት ኢትዮጵያ የምታመጥቀውን ሳተላይት አስመልክቶ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት፤ አገሪቱ የምታመጥቀው ሳተላይት ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያግዝና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡ ሳተላይት የማምጠቁ ተግባር አገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያሳየች ያለችውን ለውጥ የሚያመላክት ሲሆን፤ አገሪቱ በዘርፉ ያላትን ሚና የሚያጎላ ይሆናል፡፡

ሳተላይት የማምጠቁ ተግባር ለአገሪቱ የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነችው ‹‹ኢ.ቲ.አር.ኤስ.ኤስ1›› የተሰኘችው ሳተላይት ታህሳስ አስር 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ወደ ጠፈር የምታመጥቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia