TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ #ተፈራ_ዋልዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለለውጡ ተናግረዋል፦
.
.
“የእኔው ባልደረቦች ሁሉ ነገር እኛ በምናስበው መንገድ ነው መሄድ ያለበት ብለው ሲያስቡ የኢትዮጵያ ሙጋቤዎች ነው ያልኳቸው” አቶ ተፈራ ዋልዋ
.
.
- “ኢህአዴግ ማምጣት ያለበትን ለውጥ አምጥቷል ግን ቢያንስ 7 አመት ዘግይቷል፤ አሁን በየቦታው የተፈጠረው የግጭት ጉንፋን የዚህ መዘግየት ውጤት ነው፡፡”

- “ዐቢይ እና ዐቢይን የመሣሰሉ ጭንቅላቶች ለሀገራችን የዘመኑ ጭንቅላቶች ናቸው፡፡ ፈጥነው መሄድ የሚችሉ፣ ለውጥ ፈላጊ ጭንቅላቶች ናቸው፡፡ ለውጡ ደግሞ ተነካኪ ለውጥ አይደለም፤ ተሻግሮ የሚሄድ ለውጥን ማምጣት የሚችሉ ጭንቅላቶች ናቸው፤ ታዲያ ይሄ ኢትዮጵያን እንዴት አያሸጋግርም ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል?”

- “ይሄ ኢትዮጵያን ያበላሻል ብሎ የሚያስቡት ለኔ እዛው ድሮ የነበረ ቦታ ላይ ቆሞ የቀረ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች ናቸው፡፡”

- “ሙጋቤ ከ90 አመታቸውም በኋላ ሀገር መምራት የምችለው እኔው ነኝ ብለው ነበር፤ የእኔው ባልደረቦችም ሁሉ ነገር እኛ በምናስበው መንገድ ነው መሄድ ያለበት ብለው ሲያስቡ የኢትዮጵያ ሙጋቤዎች ነው ያልኳቸው፡፡”

- “አሁን እነ ዐቢይ የሚራመዱት ጉዞ የዘመኑ ጉዞ ነው የዘመኑ ሀይል ነው፡፡ ተገቢ ነው ይሄ ነው የበለጠ ይችን ሀገር የሚያራምደው ብሎ ማሰብ ከተሳነን እኛ ራሳችን ያለፍንበትን መርሳት ነው፡፡”
የቀድሞው አቅም ግንባታ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ማህበረሰብ የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ ስለ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ስላመጡት ለውጥ የተናገሩት!

Via አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia