TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦዴፓ⬇️

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት #ተጠናቀቀ

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በጅማ ሲካሄድ የቆየው ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ በቆይታው የፓርቲውን ስያሜ ጨምሮ የአርማ እና የመዝሙር ለውጥ አድርጓል።

በተጨማሪም የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደዚሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ምርጫን አካሂዷል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉበት
ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ ታሪካዊ ነበር ብለዋል።

በተለይም አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የመጡበት፣ የስያሜ፣ የአርማ እና መዝሙር ለውጥ የተካሄደበት መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ሊቀመንበሩ የኦሮሞ ዴሞራሲያዊ ፓርቲ ህዝቡን ለማገልገል ከዛሬ ጀምሮ #በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ይግባልም ብለዋል።

በአዲስ መንፈስና ሀሳብ ለማገልገል የተነሳው ፓርቲው በፍቅርና በአንድነት ለማገልገልም ተግቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ ሲሆን የተለያዩ አዋጆችና የዳኞችና የሬጅስትራሮችን ሹመት አጽድቋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia