TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮ ቴሌኮም እና ገቢዎች ሚኒስቴር ስምምነት !

ኢትዮ ቴሌኮም እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል #የግብር_ክፍያዎችን በቴሌብር ለመሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ዛሬ አድርገዋል።

ስምምነቱ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ደንበኞች የተለያዩ የግብር ክፍያዎችን በቴሌብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ተጠቅመው #በየትኛውም_ጊዜ እና #ቦታ ሆነው ያለምንም ውጣውረድ በኦንላይን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

አጭር መረጃ ስለ ስምምነቱ፦

- በዋናነት ለገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ግብርንና የግል ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ፣ የፌደራል ታክስ ክፍያዎችን በወቅቱ ለመሰብሰብ ያግዛል።

- የቴሌብር ተጠቃሚዎች ከግል ወይም ከድርጅት የቴሌብር አካውንታቸው በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ/ በአጭር ቁጥር *127# በመጠቀም የግብር ክፍያቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ ለመክፈል ያስችላቸዋል።

- በቴሌብር ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ከሚፈጽሟቸው ግብይቶች ከሰበስቡት ገንዘብ ላይ ለግብር ክፍያ በቀጥታ መክፈል ይችላሉ።

- በገቢዎች ሚኒስቴር ሰርቨር ላይ መረጃን ወቅታዊ በማድረግ በመዘግየት ምክንያት በግብር ከፋዩ ላይ የሚደርሰውን ቅጣት ለማስቀረት እና ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

- አገልግሎቱን ለማግኘት የሚኒስቴር መ/ቤቱ ደንበኞች ወደ www.mor.gov.et. በመግባት እና የኤሌክትሮኒክ ታክስ አገልግሎት የሚለውን በመመምረጥ፣ አስፈላጊውን ሂደት ሲጨርሱ ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚሰጣቸውን የሰነድ ቁጥር በመጠቀም በቀላሉ ክፍያቸውን በቴሌብር አፕሊኬሽን መፈጸም ይችላሉ።

- በአጭር ቁጥር *127# በመጠቀም የግብር ክፍያ የሚለውን በመምረጥ ክፍያ መፈፀም ይቻላል።

- ደንበኞች የክፍያ ደረሰኝ ወዲያውኑ በኢ-ሜል አድራሻቸው ማግኘት ይቻሉ።

Credit : አዲስ ማለዳ
Photo Credit : የገቢዎች ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
👍798👎10031😱23🕊16🙏13😢12🥰9🤔8