TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ተቸ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፤ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል። ሊቀመንበሩ በነበራቸው ቆይታ ፦ - የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ - የኑሮ ውድነት - የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ - ከሰሞኑን…
" ሁለት ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም " - ዶክተር መብራቱ አለሙ
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ፣ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ቦሮ) የውጪ እና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር መብራቱ አለሙ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲን ወክለው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በዚህ ቆይታቸው ፦
- ስለ ሰሞነኛው ምርጫ
- ስለ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የደህንነትና ሰላም ሁኔታ
- ከምርጫ ሲመለሱ ስላጋጠማቸው ነገር
- ስለ መሰረተ ልማት ጉዳይ ... ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል።
ዶ/ር መብራቱ አለሙ ከተናገሩት ፦
" በዚህ ምርጫ ላይ ህዝባችን በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ለማየት ሞክረናል።
2 ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም።
ኤሌክትሪክ ከተዘረጋ ወደ 10 ዓመታት ይሆነዋል ፤ ግን ከግጭቱ በኋላ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው አልተገነቡም። ጨለማ ውስጥ ነው መተከል ያለው።
ገዢው ፓርቲ (ብልጽግና) ደግሞ የሚበራ አምፓል ነው ያቀረበው ለምርጫ እንኳ ምልክት አድርጎ። ‘ የቆመ ፓል እንጂ ሚበራ አምፓል የለም ’ እያሉ መፈክር ያሰሙ ነበር የኛ የፓርቲ ደጋፊዎች።
የሚጠጣ ንጹህ ውሃ የለም፤ መንገድ የለም።
መተከል ዞን ማለት የህዳሴው ግድብ፣ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ፣ ሰፋፊ መሬት ፣ ከሱዳንም ጋር ረጅም ድንበር ያሉበት ዞን ነው።
ይህ ዞን እንግዲህ የመልካም አስተዳደር ፣ የመንገድ እጦት አይገባውም። የተማረ የሰው ኃይል አለው። ይሄ ማለት በክልሉ የLeadership ክፍተት አለ። ይሄንን የገዢው ፓርቲም ቢሆን አይቶ እልባት እንዲሰጠው እንደ ፓርቲ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን።
የክልሉ መንግስት በተለይ በተለይ በመሠረተ ልማት ላይ ኮሚቴ አቋቁሞ በደንብ መስራት እንዳለበት ይሰማኛል።
በተረፈ ብዙ ችግሮች አሉ። በመልካም አስተዳደር ፣ በሙስና (በተለይም ማዕድን ያለበት አካባቢ ላይ)፣ የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ በጣም ከፍተኛ ነው። ይሄ ሁሉ ችግር ተደማምሮ ህዝቡ ችግር ላይ ነው። "
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-03
#የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ? #ቦሮፓርቲ
@tikvahethiopia

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
🇪🇹የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ?🇪🇹 “ ሁለት ወራት ከ18 ቀን ነው መተከል የቆየሁት አንድ ቀን መብራት አልበራም ” - ዶ/ር መብራቱ አለሙ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ፣ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲ የውጪና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር መብራቱ አለሙ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲን ወክለው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።…
😢191❤72😭27🙏23🕊21👏20🥰15😱15😡13🤔8