TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ ኃላፊ ወይዘሮ #ብዙአየሁ_ቢያዝን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት በባለሙያዎቹ ላይ እርምጃ የተወሰደው በጥቅም ተገዢነትና #አድሏዊ አሰራርን በመፈጸም በክልሉ የገቢ አሰባሰብ ላይ ተጽዕኖ በማሳረፋቸው ነው። ባለሙያዎቹ #ግብር ተመን አሳንሶ በመገንባት፣ ተገቢው የግብር ውሳኔ ባለመወሰን፣ ለሐሰተኛ ደረሰኞች ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው አርምጃው እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል። ከባለሙያዎቹ አራተ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል ብለዋል። እንዲሁም ለ24ቱ የቃል ማስጠንቀቂያ፣ 25 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና ሌሎቹ ደግሞ ዕድገት መከልከልና የሚሰሩበትን መደብ በመቀየር እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ቢሮው በተያዘው ዓመት 12 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ያሳካው አምስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር መሆኑንም ወይዘሮ ብዙአየሁ አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1