የሀዋሳ ድምፅ FM 97.7‼️
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› #ብልሽት ምክንያት #አስር_ወራትን ያለ ሥርጭት ማሳለፉን የዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ #አርማዬ_አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት ለአስር ወራት ያህል አገልግሎት እንዳልሰጠና መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል፡፡ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዳይሰጥ የተደረገውም የመሣሪያ ግዥ ሂደቱ ሰፊ ጊዜን በመውሰዱ ምክንያት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ መሣሪያው ብልሽት በደረሰበት ወቅት በባለሙያዎች ተመርምሮ ሲጣራ መቀየር እንዳለበት ታምኗል፡፡ ማሣሪያውን ለመቀየር ዩኒቨርሲቲው ቀጥታ ግዥ ማድረግ ስለማይችል ሦስት ጊዜ ጨረታ ቢወጣም ብቸኛ የጨረታ አቅራቢ አንድ ሰው ብቻ ስለነበር እንዳይካሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህም የግዥው ሂደት ጊዜ በመውሰዱ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዲያቆም ተገልጿል፡፡
የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ያለ ሥርጭት መቆየቱ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ወይዘሮ አርማዬ፤ ጣቢያው ሲቋቋም ዩኒቨርሲቲው እየሠራ ያለውን ጥናትና ምርምር እንዲሁም መሠረታዊ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ለማድረስና ራሱን የሚያስተዋውቅበት መድረክ እንደመሆኑ አገልግሎት አለመስጠቱ መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም ተናግረዋል፡፡
የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ለጥናትና ምርምር፣ ለማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ለመማርና ማስተማር ሥራዎች ድጋፍ ስለሚያደርግ ትኩረት ተሰጥቶት መሣሪያው መገዛት እንዳለበት ታምኖ ለግዥ ኤጀንሲ ደብዳቤ በመጻፍ በውስጥ ጨረታ እንዲገዛ ፈቃድ መሰጠቱን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም አቅራቢ ድርጅቱ ውል መፈፀሙንና በቅርብ ቀናት ውስጥ ማሣሪያው ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደሚገባ፤ ለግዥውም ሦስት ሚሊዮን ብር ወጭ መደረጉን፤ የሥርጭት አገለግሎቱም በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረው፤ ከመሣሪያ ግዥው በተጨማሪ በቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ገብረጊዮርጊስ አብርሐ በበኩላቸው፤ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማኅበረሰብ ራዲዮን በሚመለከት በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት አስር ወራትን ከአገልግሎት ውጭ መሆኑ በብሮድካስት ባለሥልጣኑ በኩል እንደሚታወቅ ገልፀዋል፡፡
የጥገናና ተከላው ሥራ የባለ ሥልጣኑ ድርሻ አለመሆኑንና፤ ነገር ግን የራዲዮ ጣቢያዎች እንዲህ ዓይነት እክል ሲያጋጥማቸው በውስጥ ሙያተኞች የሚስተካል ከሆነ ሥራውን ማከናወን የሚችሉ ባለሙያዎች እገዛ እንዲያደርጉላቸው፤ በሌላ መልኩ ሥራው በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ብቻ የማያልቅ ከሆነ በተለይም መሣሪያዎች በጨረታ የሚገዙ ከሆነ ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ምክር እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድም ባለሥልጣኑ ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር ራዮ ጣቢያ ድጋፍ ማድረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
‹‹የአየር ሰዓት እንኳን አስር ወር ይቅርና አስር ሴኮንድም ቀላል አይደለም›› ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለመደ ሥርጭትና ህዝባዊ አገልግሎት ያለው ሚዲያ ከአገልግሎት ውጭ ሲሆን ተጽዕኖው ቀላል አለመሆኑን ጠቁመው፤ ህዝቡ የመረጃ ባለቤት መሆን እንዳለበትና የተቋቋመውን ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ ምንም እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ በበላይነት የያዘው ቢሆንም፤ አገልግሎቱ የህዝብን የመረጃ ማግኘት ባለቤትነት ማረጋጋጥ ጉዳይ ስለሆነ፤ ፈልገው ያደረጉት ባይሆንም ይህን ያህል ጊዜ አገልግሎት አለመስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ አመላክተዋል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia