TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተፈቅዷል! የሰቆጣ የተጠየቀው ሰልፍ ተፈቅዶዋል፡፡ በ23/10/2010 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እንደሚከሄድ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት #ብሄርን ወይም ማንነትን መስረት ካደረጉ ግጭቶች #ሃይማኖትን መሰረት ካደረጉ ግጭቶች #የግለሰብ ይሁን የመንግስት ንብረትን ለመዝረፍ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች #ቋንቋን …ባህልን…ከሌሎች አላስፈላጊ ጠባጫሪነት እራስን መከላከል ያስፈልጋል፡፡

የሰልፉ ዋና አላማ ፡ የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች በአደባባይ ማቅረብ ሲሆን፡፡ ህዝቡ/ ወጣቱ ጥያቄዎን በሰለጠነ መንገድ እና ሰላማዊ ሰልፉም ሰላማዊነቱን በጠበቀ የማድረግ ሃላፊነት አለበት፡፡ ህዝቡ እና ኮሚቴው ይህን ተከትሎ አላስፈላጊ የሆኑ ጠባጫሪነት እና አላስፈላጊ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላትን መከላከል ፤ በሰልፉን በማሰተባበር ላይ የምትገኙ የጸጥታ አካላትም ከወዲሁ ህዝቡ የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች በማስተባበር እና ጸጥታውን ከህዝቡ ጋር በመሆን እንድታስከብሩ ከወዲሁ እንጠይቃለን፡፡

ኮሚቴው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ ከተማ⬇️

ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ባለፉት 2 ወራት የተገነቡ ህገ ወጥ ቤቶች ላይ መንግስት እርምጃ ወስዷል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ህዝቡን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ለመውሰድ አንዳንድ አካላት በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ትክክል ያልሆነ መረጃ እያሰራጩ እንደሚገኝ ተደርሶበታል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቤቶች ፈርሰዋል ወደ ተባለበት ቦታ ደውዬ ከአካባቢውን ነዋሪ ጋር ቆይታ አድርጌ ነበር ነዋሪው በሰጠኝ መረጃ ዛሬ የተወሰደው እርምጃ ምንም አይነት #ብሄርን መሰረት ያደረገ እንዳልሆነ አስረግጦ ነግሮኛል። በፌስቡክ የሚወሩ ወሬዎችም ህዝብን ለማጋጨት የታሰበባቸው በመሆኑ የከተማው ህዝብ በአንድነት ሊያወግዘው ይገባል ብሏል።

ነዋሪው እንደገለፀልኝ እውነት ህጋዊ ቤቶች ፈርሰው ከሆነ ለአስተዳደሩ ያሉትን ማስረጃዎች አቅርቦ መፍትሄ ማግኘት እየተቻለ የከተማው ሰላም ለማደፍረስ እና በሰላም እየኖረ ያለውን ህዝብ ለማጋጨት የሚሰራው ስራ ሊቆም ይገባል ሲል ገልፆልኛል።

ከቀናት በፊት ዶክተር አብይ አህመድ በሰጡት መግለጫ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ መንግስታቸው ቁርጠኛ እንደሆነ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

©F- ህገ ወጥ ቤቶች ፈርሰዋል በተባለበት ቦታ ነው የሚኖረው ተጨማሪ ከራሱ አንደበት መስማትም የምትፈልጉ ካላችሁ ስልኩን ሰጣችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ‼️

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሰኞ ምሽት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የተማሪዎችን ማደሪያዎች መብራት ካጠፉ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ስድስት ተማሪዎች ቆሰሉ። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በኹከቱ የሞቱ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ማግኘታቸውን አረጋግጧል። የመማር ማስተማር ሒደቱ ግን ዛሬም እንደተቋረጠ ነው።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንፃራዊ በሆነ ሰላም የዘንድሮውን አመት የመማር ማስተማር ስራ ሲያከናውን የቆየው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በጊቢው በተፈጠረ ሁከት ሰላማዊ ድባቡን ጠፍቷል፡፡ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውም በበተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ተቋርጧል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው አለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር #አለማየሁ_ዘውዴ ትናንት ምሽት ያልታወቁ አካላት በተማሪዎች መኖርያ አካባቢዎች መብራቶች በማጥፋት ባደረጉት እንቅስቃሴ ሁከቱ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ትናንት ምሽት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል በአንዳንድ ተማሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚነገረው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በተማሪዎች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት አለመድረሱን አስረድተዋል ፡፡

ዶ/ር አለማየሁ "ያልታወቁ" በሚል ለተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ መነሻ ያሏቸው አካላት በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ወይም ከዚያ ውጭ የመጡ ስለምሆናቸው ለተነሣው ጥያቄ በፀጥታ አካላት ምርመራ እየተካሄደበት ከመሆኑ ውጭእስካሁን የታወቀ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራው እንደተቋረጠ ነው፡፡ ሁከቱን በመሸሽ ግቢውን ጥለው የወጡ ተማሪዎችም ብዙ ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮቸ፣ የተማሪ ተወካዮችና የአስተዳደሩ ከፍተና የስራ ሀላፊዎች ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት የተቋረጠው ት/ት #በአፋጣኝ ከነገው ዕለት ጀምሮ እንዲጀመር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡

አንዳንድ ወገኖች እንደሚገልፁት በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ #ብሄርን መሰረት ያደረገ ገፅታን የተላበሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia