TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ብሄራዊ_ቤተ_መንግስት

የ2011 በጀት ዓመት የታማኝ የግብር ከፋዮች የሽልማትና የእውቅና መድረክ በብሄራዊ ቤተ-መንግስት ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ፕሮግራሙን ታድመዋል።

“ሀገረን መውደድ በተግባር ነው” በሚል መሪ ቃል ነው መርሃ ግበሩ የተካሄደው። ወ/ሮ አዳነች በመክፈቻ ንግግራቸው በ2011 በጀት ዓመት 198.2 ቢሊዮን ብር የግብር ገቢ መሰብሰቡን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችም 1.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንም ተናግረዋል። በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ በታማኝ ግብር ከፋይነት ለተመረጡ 163 ተቋማት በዕለቱ የክብር እንግዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አማካይነት እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia