TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባሌሮቤ

ትላንት በባሌ ሮቤ ቁጥራቸው ውስን የሆኑ ወጣቶች የታሰሩ ፖለቲከኞች (አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ሃምዛ ቦረና... ሌሎችም) ይፈቱ በሚል ሰልፍ በሚያደርጉበት ወቅት ከመንግስት የፀጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት 'አወል አብዱሮ' የተባለ ወጣት መገደሉን የባሌ ሮቤ ቲክቫህ አባላት አረጋግጠዋል።

የወጣቱ አወል የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት መፈፀሙን አዲስ ስታንዳደርድ ድረገፅ አስነብቧል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ትላንት የታሰሩ እና የተጎዱ ወጣቶች ስለመኖራቸው ከድረገፁ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

PHOTO : ADDIS STANDARD
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia