TIKVAH-ETHIOPIA
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ፤ " ውሉ የተቋረጠው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው " ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። " የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ' እንከፍላለን ' ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም " ሲልም ገልጿል። ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ግብር ለመክፈል ወደኋላ የሚል…
#ቢጂአይ #ፐርፐዝብላክ
" ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ
" የመመለስ አለመመለሱ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " - ቢጂአይ ኢትዮጵያ
ስምንት ወራትን የፈጀውና ያለስኬት የተጠናቀቀው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደት አሁን ላይ ወደ ክስ ሂደት አምርቷል።
ገዢ ሆኖ የቀረበው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ ጊዜያዊ የእግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍለት ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል።
የእግድ ጥያቄው ምን ይላል?
- ተጠሪ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ውሉን እንዳያቋርጥና እንዳይጥስ ታግዶ እንዲቆይ
- በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ፤
- ለሽያጭ የቀረበው በአጠቃላይ ስፋቱ 29 ሺህ 896.51 ካ.ሜ የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ " በውላችን አንቀጽ 6 መሰረት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ቀርቦ ውሉን መፈረም ሲጠበቅበት ውሉን አቋርጫለው ክፍያውንም አልመልስም ሲል የህዝብና የደሃ ማኅበረሰብን ገንዘብ ከህግና ከሥርዓት ውጪ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ውሉን አቋርጧል፤ ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ሲል ገልጿል
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሐሙስ የካቲት 28 ዕለት በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ የህግ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ነጋ ምህረቴ " ገንዘቡን የመመለስ ያመመለስ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።
ተጨማሪ መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የቢጂአይ የኮርፓሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በኃይሉ አየለ " ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ አስተያየት አይሰጥም " የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
የፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ምን ይላል ?
በብሔራዊ ባንክ ስር በሚተዳደሩ ማንኛውም ባንክ በተጠርጣሪ ስም ያለ እስከ 1ቢሊዮን 519 ሚሊዮን ብር ሳይንቀሳቀስ ታግዶ እንዲቆይ እና የክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ተጠሪ ውሉን እንዳይቋረጥ እና እንዳይጥስ የቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው ሲሆን ለዚህም "የውሉ ህጋዊነት ክርክር የሚያስነሳ ስለሆነ አመልካች (ፐርፐዝ ብላክ) ተጠሪ ውሉን እንዳይጥስ የጠየቀውን እግድ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም" ሲል በትዕዛዙ ላይ ጠቅሷል።
ይህ የእግድ ውል የሚቆየው ለ20 ቀናት (እስከ መጋቢት 17) ወይም ከግራ ቀኙ አንዱ አቤቱታ ሲያቀርቡ መሆኑን የካቲት 28 ስምት ቀን ባሳለፈው ትዕዛዝ ጠቅሷል።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia