#AddisAbaba
" የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም ዝውውር አይደረግም " - ኤጀንሲው
በአዲስ አበባ 7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ እና ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።
ማረጋገጥ እና ምዝገባው ለመጪዎቹ 5 ወራት ይቀጥላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ ከዚህ በፊት በ6 ዙር ባደረገው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ምዝገባ ከ383,000 በላይ ይዞታዎች አረጋግጦ በካዳስተር ሲስተም መመዝገቡን አሳውቋል።
ኤጀንሲው ምዝገባው መካሄዱ አንድ ይዞታ በማን፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደተያዘ እና በይዞታው ላይ ለተፈጠረው መብት ህጋዊ ዋስትና አና ከለላ በመስጠት የመሬት ነክ ገበያውን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል ብሏል።
7ተኛ ዙር የይዞታ ማረጋገጡ ምዝገባ በ7 ክፍለ ከተሞች ይካሄዳል የተባለ ሲሆን 85 ቀጠናዎች እና 386 ሰፈሮችን ያካትታል።
ምዝገባው የማያካሄዱ ባለይዞታዎች ምንም አይነት ህጋዊ ዋስትና እና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቆ ባለይዞታዎች እና በይዞታዎች ላይ ጥቅም አለን የሚሉ ሁሉ በምዝገባው ላይ ሊሳተፉ ይገባል ብሏል።
ምዝገባው እስከ ሚያዝያ 28 ድረስ ባሉት 5 ወራት የሚካሄድ ሲሆን ከ15 ቀናት በኋላ ጀምሮ ባለይዞታዎች አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመሄድ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ለማመልከት ሲኬድ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ሲሆን የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት የከናወናል።
የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም ዝውውር እንዳማይደረግ ተገልጿል።
7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች፦
* ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣ 5፣ 8፣ እና 10
* የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ 5፣6፣7 ፣8 እና 9
* ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣5፣11፣12እና14
* አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣5 እና 8
* ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣3፣4፣5እና 6
* አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ11፣12፣13እና 14
* ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 እና 13 ናቸው ተብሏል።
የይዞታ ማረጋገጡ ስራ የሚከናዎነው በስልታዊ ዘዴ ወይም በመደዳ ሲሆን የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በታወጀባቸው በ7 ክፍለ ከተማዎች እና በ30 ወረዳዎች ውስጥ በ85 ቀጠናዎችና በ386 ሰፈሮች የይዞታ ማረጋገጥ ስራው ይካሄዳል።
በተጠቀሰው አካባቢ ባለይዞታ የሆኑ ሰዎች #በጊዜ እንዲያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳስቧል።
@tikvahethiopia

😡275❤212🙏46😭44👏29🥰25😢18🕊18😱14