ብራዚል‼️
ብራዚል ውስጥ ሥራ ላይ የነበሩ 430 ሐኪሞች ሥራቸዉን አቋርጠዉ ወደ ሃገራቸዉ ወደ ኪዩባ ተመለሱ። በብራዚል በሕክምና ዘመቻ ላይ የነበሩት እነዚህ የኪዩባ የሕክምና ባለሞያዎች በድንገት ሥራችሁን አጠናቃችኋል የተባሉት በአዲስ ተመራጩ የብራዚል ፕሬዚዳንት #በዣር_ቦልዞናሮ እና በኩዩባ መንግሥት መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት መሆኑ ታዉቋል። 8300 የኪዩባ ሐኪሞች «ተጨማሪ የሕክምና ባለሞያ» «Mais Médicos» በተሰኘ የመንግሥት ስራ መርህ ግልጋሎት ለመስጠት ነዉ ወደ ብራዚል የመጡት። ኩባውያኑ የብራዚል ሐኪሞች ጋር የሕክምና ባለሞያ እጥረት በሚታይባቸዉ የብራዚል አዉራጃዎች ዉስጥ ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia