TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት የርክበ ካህናትጉባኤ ነገ ግንቦት 2 ቀን 2015  ዓ/ም ይከፈታል። በአሁን ሰዓት የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሔድ ላይ ነው። ፎቶ ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ @tikvahethiopia
#Update

የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል።

ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል።

ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል " ሲሉ ገልጽዋል።

" የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ " ጌታችን፡- ' እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ ' ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል " ብለዋል።

በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በተለይም #በትግራይ እና #በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል " ብለዋል።

" በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል " ሲሉም አክለዋል።

" እኛ ያጐደልነው ፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያኩ " ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia