TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢሶዴፓና ኢዜማ በስያሜ መወዛገብ ጀመሩ!

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ስያሜ በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መወሰዱን የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለፁ። የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናዔል ፈለቀ በበኩላቸው የፓርቲያቸው ስያሜ ከማንም ፓርቲ ጋር እንደማይገናኝ ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር በየነ ኢዜማ…የሚባለው ቡድን “ማ” የምትለዋን ፊደል ማህበራዊ ፍትህ ብሎ ይተረጉማል። ይህ ትርጓሜ ሶሻል ዴሞክራሲ ከሚለው የፓርቲያችን ስያሜ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ተቃውመናል፤ ቅሬታችንንም ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርበናል ብለዋል።

ፕሮፌሰር በየነ ‹‹የኢዜማን ዝርዝር ፕሮግራም #ባናውቅም ስያሜው ከእኛ ፓርቲ ጋር ተመሳሳይ ነው። በዚህም ህብረተሰቡን እያሳሳቱ ናቸው። #በኢዜማ ውስጥ የተካተቱት እንደ ሰማያዊና ኢዴፓ የመሳሰሉ የፓርቲ አባላት የሊብራል አራማጆች ናቸው። አሁን ሃሳብ አለቀባቸው መሰለኝ ማህበራዊ ፍትህ ይላሉ። የፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ተመሳሳይ ስያሜ ያላቸውን ፓርቲዎች ስለሚከለክል መጠሪያው እንዲከለከልልን ጥያቄ አቅርበናል›› ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናዔል (ኢዜማ) የሚለው ስያሜ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ይመሳሰላል የሚል እምነት የለንም። እስካሁን ለፓርቲውም ሆነ ከምርጫ ቦርድ የቀረበ ቅሬታም ሆነ ሌላ አስተያየት የለም፤ ቅሬታ ያቀረበ ካለ በህጋዊ መንገድ ታይቶ ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-07

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia