* የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት !
በአፋር ክልል ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ።
የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት በከፍተኛ የውጭ ማንዛሬ በማስገባት የማስፋፊያ፤ የመልሶ ግንባታ እና አዳዲስ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በማከናወን የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ነገር ግን በአንዳድ የክልሉ ከተሞች በተለይም #በአይሳኢታ እና #ዱብቲ ከስኳር ፋብሪካው ጋር የተመሰረቱ መንደሮች እንዲሁም ለውሃ አግልግሎት የሚሰጡ ትራንስፈርመሮች እና የኤሌክትሪክ ሽቦና መለዋወጫ ላይ አሁን ባለው ዋጋ 3.9 ሚሊዮን ብር በላይ ስርቆት ተፈፅሟል።
ተቋሙ ፤ ጉዳዩ በህግ ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ የጠቆመ ሲሆን የችግሩን አሳሳቢነትም በመረዳት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገዙና ከፍተኛ የህዝብ ሃብት የፈሰሰባቸው በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ እንደራሱ ንብርት ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል ብሏል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው የኤሌክትሪክ የመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦችን በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ አልያም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በስልክ ቁጥር 👉 0913834455 ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
@tikvahethiopia