TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ፦

ለህዝብ ጥያቄ ክብር የሌለው ድርጅት ሊመራ አይችልም!

በሀገራችን ዜጎች ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሎበት በተዘጋጀዉ የህጎች ሁሉ የበላይ በሆነ ህገ መንግሥት መሠረት የተጠየቀው የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት መብት #በአምባገነኖች እየተደፈጠጠ እስከ ለውጥ ምልክት መባቻ ድረስ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጣ የተባለውን ለውጥ መሠረት በማድረግ ለዘመናት ሲነሳ የነበረውን የሲዳማ ህዝብ ክልል ሆኖ የመደራጀት መብት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሶ ባለበት በዚህ ወቅት ከዚህ ቀደም አንደሰጋነው ሁሉ ደኢህዴን ለውጡን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ በድጋሚ የህዝብ ጥያቄ የሚክድና የሲዳማን ህዝብ የሚንቅ መወያያ ሰነድ አቅርቦ እየፈነጨ እንደሆነ ድርጅታችን ይገነዘባል፡፡

በመሆኑም በትናንትናው እለት ማለትም የካቲት 28 ቀን 2011ዓ.ም ደኢህዴን ባደረገው የአመራር ስብሰባ ላይ የሲዳማን ብሔር የሚያንቋሽሽ እና የህዝባችን ለዘመናት የከፈለውን መስዋዕትነት የዘነጋና የካደ ሰነድ ድርጅታችን እጅግ አጥብቆ እየተቃወመ በዚህ ምክንያት እስከ አሁን በሀዋሳና አካባቢዋ ለተከሰተውና ለሚከሰተው ለማንኛውም ክስተት የህዝብን ስሜት ቀስቃሽና ከሃጅ የሆነ ሰነድ አዘጋጅ ደኢህዴን ኃላፊነት እንደሚወስድ ድርጅታችን አጥብቆ ያሳውቃል፡፡

መላዉ የሲዳማ ህዝብም በደኢህዴን ጣልቃ ገብነት የተቀሰቀሰዉ ቁጣ ሌላ መልክ እንዳይይዝና በመካከላችን የሚኖሩትን ሌሎች ህዝቦችን ስጋት ላይ በማይጥል መልኩ በሰከነና በተለመደዉ ባህላዊ ሥርዓቱ እየተደማመጠ ተቃዉሞዉን እንዲያሰማና እንዲያደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

ድርጅታችን ሲአን የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ በህገ መንግሥቱ ብቻ ምላሽ እንዲሰጠዉ ቀደም ስል ባወጣ መግለጫችን በተደጋጋሚ መጠየቁ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በድጋሚ ደኢህዴን ከዚህ ፀረ-ህዝብ ድርጊት እጁን እንዲሰበስብ አጥብቀን እያሳሰብን ድርጅታችን ሰላማዊ የመሪነት ሚናዉን በፅናት ለመወጣት መዘጋጀቱን እንገልፃለን፡፡

የካቲት 29 ቀን 2011ዓ.ም
ሲዳማ አርነት ንቅናቄ
ሀዋሳ፣ሲዳማ፣ ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia