TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ሙርሲ #ተገደሉ እንጂ የተፈጥሮ ሞት አልሞቱም" ፕሬዘዳንት #ረሲፕ_ጣይፕ_ኤርዶጋን
.
.
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዘዳንት የነበሩትና እ.አ.አ በ 2013 #በመፈንቀለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱትን #ማሃመድ_ሙርሲ አሟሟትን በተመለከተ የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን የሰጡት አስተያየት ሃላፊነት የጎደለው ስትል ግብፅ ኮነነች፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ኤርዶጋን የሙርሲን አሟሟት በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የግብፅ መንግስት የሙርሲን ህይወት ለመታደግ ምንም አይነት የወሰደው እርምጃ የለም የሚለው አስተያየት ተገቢነት የጎደለውና መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ኤርዶጋን ትላንት በተደረገው የምርጫ ዘመቻ ሰልፍ ላይ ሙርሲ “ተገደሉ እንጂ በተፈጥሮ ሞት አልሞቱም ”ብለው ሲናገሩ በቴሌቭዥን ተደምጠዋል፡፡

ኤርዶጋን አክለውም “ሙርሲ ለ20 ደቂቃ መሬት ላይ ወድቀው ሲያጣጥሩ ቢቆዩም ህይወታቸውን ለማዳን የሞከረ ግን አልነበረም”ማለታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡-ፕሬስ ቲቪ
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwdeode @tikvahethiopia