TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ በዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ #በመደርመሱ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ በተመለከተ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ፦

- አራት መቶ አስራ አምስት (415) ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ ተደርምሷል።

- የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው አልፏል።

- በድልድዩ መደርመስ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ተጎጂዎች  በሪፌራል፣ ያኔት፣ አላትዮን፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

የተማሪ ወላጆችም ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች በጥዋቱ ያልተጠበቀ አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻሉ ገልጾ ፤ በሁኔታው ተደናግጠው ከግቢ የወጡም ሆኑ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደነበሩበት እንዲመለሱና ለነገ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስቧል።

@tikvahethiopia