TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቅርቡ የመከስከስ አደጋ በደረሰበት የበረራ ቁጥር 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁ አንዲት ፈረንሳዊት የቦይንግ ኩባንያ በትንሹ የ276 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ይከፍላቸው ዘንድ ክስ መስርተዋል።

Nadege Dubois-Seex የተባሉት ወይዘሮ ክሱን የመሰረቱት በአሜሪካዊው የሕግ ጠበቃቸው ኖማን ሁሴን በኩል ነው። ጠበቃ ሁሴን እንደሚሉት በኢንዶኔዢያና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ላይ የደረሰው አደጋ ሙሉ በሙሉ በቦይንግ ሶፍትዌር ችግር ጋይ የተያያዘ መሆኑን የአሜሪካ አቪዬሺን ባለስልጣንና በመጨረሻም የቦይንግ ኩባንያ ያረጋገጡትና ያመኑበት ጉዳይ በመሆኑ ፤ ባልተሟላ ሶፍትዌርና የበረራ ማኑዋል ምክንያት ለደረሰው አደጋ ኩባንያው ለደንበኛዬ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በካሳ መልክ መክፈል አለበት ሲሉ ፓሪስ ላይ ለተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

√በተመሳሳይም #በኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸው ሕይወታቸውን ያጡባቸው የቦይንግ ኩባንያን #በመክሰስ የካሳ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1