TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል።

ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ መረጃ ተለዋውጥናል።

በየጊዜው የነበሩ እጅግ ዘግናኝ ከህግ ሆነ ከሞራልም ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ወደ ኃላ ተመልሰን ለመዘርዘር ጊዜውም አይበቃን ፤ በተለይም ከቲክቫህ ጋር ዓመታትን ያሳለፋችሁ የምታውቁት ነው።

ሌላው ይቅር በቅርብ ጊዜ እንኳን ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተነሳ በኃላ እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ቪድዮዎች ተሰራጭተው ስለጉዳዩ መረጃ መለዋወጣችን የቅርቡ ትውስታችን ነው።

ዛሬ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተሰራጨው አሰቃቂ ቪድዮ በርካቶችን ያስደነገጠ ያሳዘነ ሆኗል። ቪድዮውን እዚህ አምጥቶ ማጋራት ትክክል እንዳልሆነ ታውቁታለቹ ፤ በጥቅሉ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሰው ልጅ #በህይወት_እያለ በእሳት እንዲቃጠል ሲደረግ የሚያሳይ ነው።

ከቪድዮው ጋር በተያያዘ እነማን ? መቼ ? የት ? እና እንዴት ? ስለሚለው ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል አካል በአስቸኳይ ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅበታል።

በተለይም ደግሞ በቪድዮው ላይ የፀጥታ ኃይሎችን የደንብ ልብስ ያደረጉ ሰዎች በግልፅ ስለሚታዩ ተቋማቱ ማብራሪያ መስጠት አለባቸው።

የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ሊከታተሉትና ለህዝብ ሊያሳውቁ ይገባል።

እንዲህ ያለው ነገር በቪድዮ አደባባይ ላይ ሲወጣ መነጋገሪያ ይሆናል እንጂ ያልተቀረፀው ፣ ህዝብ ያላወቀው ስንት ጉድ ይኖር ይሆን ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

@tikvahethiopia
👍2.58K😢1.7K😱124👎8964👏38🥰11