TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቀበሮሜዳ

" 97 በመቶ የምንሆነው ሰፈራ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ያለፍላጎታችን ወደ ነበርንበት ቦታ እንድንመለስ እየተገደድን ነው " - ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች

" አንመለስም ካሉ ማንም አያስገድዳቸውም እኛ ግን እርዳታ አናቀርብም " - የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

በጸጥታ ችግር ከኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አዘዞ ክፍለ ከተማ አካባቢ ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ " 97 በመቶ የምንሆነው ሰፈራ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ያለፍላጎታችን ወደ ነበርንበት ቦታ እንድንመለስ እየተገደድን ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

የመጠለያ ካምፑ አስተባባሪ አቶ መላሽ ታከለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለፃ ፤ " ከኦሮሚያና ከሁመራ፣ ማይካድራ ያሉ ሰዎች ' ትመለሳላችሁ የሚል ነገር አለ ' የሰማነው ውይይትም የለም። ' ስንሄድ መሠረታዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ መሟላት አለባቸው ' የሚል ሀሳብ ነው ያለው ከተፈናቃዮቹ " ብለዋል።

የማኅበረሰቡ ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ፦ አይ.ኦ.ኤም (IOM)፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በካምፑ ጥናት አድርገው እንደነበር የገለጹት አስተባባሪው፣ " ማኅበረሰቡ አንድ ቦታ ላይ ሰፍረን ሰርተን እንቀየራለን የሚል ፍላጎት ነበረው፣ እንዲያውም ከ100ው 97 ፐርሰንቱ ሰፈራ ፕሮግራም ነው መርጦ የነበረው " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ለገሰ፣ " እነዚህ ሰዎች እንዲመለሱ ውይይት ጀምረናል፤ አንመለስም ካሉ ማንም አያስገድዳቸውም እኛ ግን እርዳታ አናቀርብም " ብለዋል።

" ምክንያቱም የእነዚህ ሰዎች መሬታቸው፣ ቤታቸው፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ያለው ከተፈናቀሉበት አካባቢ ነው። መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ ነው የሚያደርገው፣ የትኛውም ድጋፍ ቋሚ አይደለም። ይሄ ተያይዞ ክልሉንም ሰዎቹንም ወደ ድህነት የሚወስድ ስለሆነ በቀጣይ እነዚህ ሰዎች አምነው ወደመጡበት ቄዬ ይመለሳሉ " ሲሉ አክለዋል።

ከትግራይ ክልል ከመቐለ ፣ ከሽሬ ፣ ከዓዲግራት፣ ከዓድዋ የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ የተፈናቀሉ አሉ ያሉት አቶ ወንድወሰን፣ " ወደዛ የሚሄዱትን በተመለከተ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በቀጣይ መነጋገር ይጠይቃል " ነው ያሉት።

ምክትል ኃላፊው አክለው ፣ " ከወልቃይትና  ከሁመራ የተፈናቀሉት በጦርነቱ ወቅት ከሞት የተረፉ ስልሆኑ ችግሩ ዳግም የሚመለስ እየመሰላቸው ወደዛ መሄድ ትንሽ ያዝ ያደርጋቸው ካልሆነ በስተቀር ቀጠናው አስተማማኝ ነው " ብለዋል።

ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ ያሉ ተፈናቃዮች ያወያያቸው አካል እንደሌለ በገለጹት መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአቶ ወንድወሰን እውነታው ምንድን ነው ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፤ ተፈናቃዮች ያሉባቸው ካምፖች ብዙ ከመሆናቸው አንፃር ገና ቀበሮ ሜዳ እንዳልሄዱ፣ በዕቅዱ መሠረት እንደሚሄዱ፣ በደብረ ብርሃን፣ ሰሜን ሸዋ መጠለያ ጣቢያዎች ተፈናቃዮችን ማወያየት እንደጀመሩ፣ ተፈናቃዮችም በአፋጣኝ ለመመለስ ፈቃደኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ወደ ኦሮሚያ ክልል ተመለሱ ተብለናል ያሉ ተፈናቃዮችን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያም፣ ከኦሮሚያ ክልል አኳያ ያለውም እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉበት አካባቢ የጸጥታ ኃይሉ ተጠናክሮ፣ አካባቢው ከሸኔ ጸድቶ ከሆነ፣ ተፈናቃዮቹ እንደሚመለሱ ነው የገለጹት።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተጠናቅሮ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
😢314😡13386👏25😭23🕊21🥰16🙏5😱4