TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ችሎት

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል። ፖሊስ #በተጠርጣሪዎቹ ላይ #ቀሪ የምስል፣ የድምፅ፣ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ግን እስከአሁን አራት የጊዜ #ቀጠሮዎች መሰጠታቸውንና መርማሪ ፖሊስም በማስረጃ አሰባሰብ ሂደት አከናወንኩ ያላቸው ስራዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን በመጥቀስ የቀረበውን ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ዉድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኗል። ተጠርጣሪዎቹ ለነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርቡም አዟልም።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia