TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update መግለጫው ተሰርዟል⬇️

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር #ስመኘው_በቀለን አሟሟት እና የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ምርምራን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ #ተሰረዘ። መግለጫ የተሰረዘው የፌደራል ጠቅላይ ዋና አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ #አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ ባልደረባ ለዲ ደብሊው እንደተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሄዳቸው መግለጫው ለሌላ ጊዜ #ተላልፏል።” መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ቢነገርም ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልተነገረለትም። በዛሬው መግለጫ የኢንጂነር ስመኘው #አሟሟት እና ከሰኔ አስራ ስድስቱ ቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።

ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ሲዘዋወር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. ይሰጣል ተብሎ የነበረው መግለጫ ወደ ዛሬ ጳጉሜ 1 መተላለፉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1