TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአሜሪካ #ሴኔት በመላው አሜሪካ " ቲክቶክ" ን ሊያግድ የሚችል አዋጅ ትላንት ለሊት አጽድቋል።

ከቀናት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት " ቲክቶክ " እንዲታገድ ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ይታወሳል።

ትላንት ለሊት የአሜሪካ ሴኔት ተሰብስቦ " ቲክቶክ " ከቻይና ካልተፋትና ድርሻው በ9 ወር ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ አዋጅ አጽድቋል።

ቀጣዩ ሂደት ፕሬዜዳንቱን ይመለከታል።

ይህ አዋጅ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ  ባይደን የተመራ ሲሆን እሳቸው ቀደም ሲል " ይህ አዋጅ እኔ ጋር ይድረስ እንጂ ፊርማዬን አኑሬበት ሕግ ሆኖ ይተገበራል " ብለው ነበር።

አሁን በአሜሪካ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " የመታገዱ ነገር እውን እየሆነ የመጣ ሲሆን ሂደቱ ረጅም ወራትን ሊወስድ ይችላል።

በሌላ በኩል ፥ ሴኔቱ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅልን አፅድቆታል።

@tikvahethiopia