ኮሎኔል ሰጠኝ ካሕሳይ‼️
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖሊስ በኮሎኔል #ሰጠኝ_ካሕሳይ ላይ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ኮሎኔሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሜቴክ የስራ ኃላፊ የብርጋዴል ጄኔራል ሀድጉ ጌቱን መረጃ ለማሸሽ በጸሀፊው አማካኝነት ሞክሯል በሚል ተጠርጥረው ነው።
ፖሊስ ኮሎኔል ሰጠኝ ካህሳይን በተጨማሪ የሙስና ወንጀል የጠረጠራቸው መሆኑን አስታውቆ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ትናንት ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።
ፖሊስ በትናንቱ ችሎት እንደገለጸው ኮሎኔል ስጠኝ ኮሞቹ ኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ በተሰኘ ተቋም የሰው ሀብት ልማት ኃላፊ ሆነው ህግን ባልተከተለ መልኩ የ15 ሚሊዮን ብር ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ በአገርና በሕዝብ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ተጠርጥረዋል።
ኮሎኔል ስጠኝን በሙስና የጠረጠራቸው በደረሰው ጥቆማ መሰረት መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።
ከትናንት ጀምሮ የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ ዛሬ ከሠዓት በኋላ ባስቻለው 10ኛ ወንጀል ችሎት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikahethiopia