TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ? - ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች። - ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል።…
የዩክሬን ቀውስ አስከፊውን የዓለም ጦርነት ይዞ እየመጣ ይሆን ?

🇷🇺 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 🗣

" ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል። የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው። "

🇺🇦 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ 🗣

" ሩሲያ በማንኛውም ቀን አውሮፓ ውስጥ #ትልቅ_ጦርነት ልትጀምር ትችላለች። ሩሲያውያን እርምጃውን ሊቃወሙት ይገባል። ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ፤ ውጤቱ ዝምታ ሆነ። ሩሲያ ወደ 200 ሺ የሚጠጉ ወታደሮችና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር አሏት። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ ነው ስለሆነም ጥቃቱን ሊቃወሙ ይገባል "

🇺🇳 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 🗣

" ፕሬዝዳንት ፑቲን በ #ሰብኣዊነት_ስም ጦርህን ወደ ሩሲያ መልስ። ይህንን ካላደረክ ውጤቱ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት ሊያስከትል ይችላል "

🇺🇸 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 🗣

" ሩሲያ #በዩክሬን ላይ በምትፈጽመውን ወረራ ለሚደርሰው ጥፋትና ውድመት ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያድርግ ይገባል። የዓለም ህዝብ በሩሲያ ጥቃት ጉዳት የሚደርስባቸው ዩከሬናውያንን በጸሎት ያስባል። "

🇬🇧 የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን 🗣

" ሩሲያ ደም አፋሳሹን መንገድ መርጣለች፤ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ አንዋር መስጂድ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ በአሁን ሰአት አንዋር መስጂድ እንደሚገኙ ተገልጿል። ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በሰዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች እንዳይባባሱ እና በመስጂዱ ጊቢ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ሲል ከፍተኛ…
#Update

በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ መቆየታቸው ተሰምቷል።

በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉም ተብሏል።

ታላቁ አንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።

ከሁሉም ነገር በፊት #ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይልም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

(ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)

@tikvahethiopia