TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬዳዋ🔝

ሰባተኛው የመከላከያ በዓል እንደ #ምስራቅ_ዕዝ ማጠቃለያ ዛሬ በድሬደዋ ስቴድየም በወታደራዊ ትርዒት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የሀረሪና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን ጨምሮ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባና የምስራቅና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪዎች በእንግድነት ተጋብዘዋል።

©Dogl.(TIKVAH-ETHIOPIA)
#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምስራቅ_ዕዝ

የህብረተሰቡን #ሰላምና #ደህንነት የማስጠበቅ ስራን እንደሚያጠናክር የምስራቅ ዕዝ አስታወቀ። የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራን በተጠናከረ መልኩ እንደሚያስቀጥል በሀገር መከላከያ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ አስታወቁ።

ዋና አዛዡ ዛሬ በጅግጅጋ ገርባሳ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የመካከለኛ አመራሮች ስልጠና በተጀመረበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ሰላም የሚያውኩ አካላትን በመከላከሉ ረገድ ሰራዊቱ ከነዋሪው ጋር በመሆን የሚጠበቅበትን ግዳጅ ተወጥቷል።

“በአሁኑ ወቅትም በቀጠናው የተለያዩ የጸብ አጫሪነትና የጸረ ሰላም ተግባር ሲፈጠሩ ሰራዊቱ ከክልል የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላምን የማስከበር ስራ እያከናወነ ይገኛል” ብለዋል። በዚህም የቀጠናው የሰላም ሁኔታ ከዓመት ዓመት መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርቡ በቀጠናው አንዳንድ ከተሞች በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ለማሰማት ዜጎች ወደ አደባባይ የወጡበትን አጋጣሚ በመጠቀም የራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ የሞከሩ ጥቂት ግለሰቦች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ይህም ህብረተሰቡ በብሔርና በሃይማኖት ግጭት ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ እንደነበረ ጠቅሰዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia